ዲዛይን ማድረጊያ መሳርያ
ዲዛይን ማድረጊያ መሳርያ
ይህ መገልገያ በውስጡ በከተማ ልማት እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር መሪነት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና የትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በUN-Habitat፣ UN Road Safety Fund፣ እና Institute for Transportation and Development Policy ከፍተኛ ድጋፍ የተዘጋጁ የብሄራዊ የከተማ ጎዳና ዲዛይን መመርያ ቁልፍ ይዘቶችን ያካተተ ነው።
መመሪያውናውና በውስጡ የተካተቱት የኦንላይን መሳሪያዎች (ቱሎች) መንገዶችን ዲዛይን በማድረጉ ረገድ ለሁሉም ተጠቃሚዎች እንዲያገለግሉ ማለትም እግረኞችን፣ የብስክሌት ተጠቃሚዎችን ፣ የህዝብ ትራንስፖርት ተጓዦችን፣ ሞተረኞችን እንዲሁም የዕቃ ማጓጓዣዎችን ጨምሮ ለሁሉም ምቹ የሆነ ዲዛይን እንዲጎለብት ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
የጎዳና መረብ እቅድ ማውጣት
ውጤታማ የሆነ የጎዳና መረብአውታረ መረብ ለበርካታ ተጠቃሚዎች የትስስር አውታርን የሚፈጥር ነው፡፡ የጎዳና መረብ አውታረ መረብ ለእግረኞች እና ለብስክሌት ተጠቃሚዎች የተሻለ ትስስርን ከመፍጠራቸው ባሻገር ለህዝብ ትራንስፖርት የተሳለጠ አገልግሎትና ፍጥነቱ የተወሰነ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር በማድረግ የሚያግዝ ነው፡፡
ለተሟላ የአውታረ መረብአውታረ መረብ አገልግሎት መጀመሪያ የሚሆኑት የህዝብ ትራንስፖርቶች ሲሆኑ እነዚህም እንደ ፈጣን አውቶብስ ትራንስፖርት ወይም የቀላል ባቡር ትራንስፖርት ኮሪደሮች ወይም የህዝብ የታክሲ መስመሮች ናቸው፡፡ የተሟሉ ጎዳናዎች እና የእግረኞች መጓዣ መንገድ ለህዝብ ትራንስፖርቶች ማቆሚያ የተሻለ ምቾትን የሚሰጡ ናቸው፡፡ የአረንጓዴያማ ጎዳና አውታረ መረብ አውታረ መረብ የእግርእና የብስክሌት ጉዞዎችን በመደገፍ ከፍተኛ ጥራት ያለው የመዝናኛ ቦታዎችን ያቀርባል፡፡ የብስክሌት መንገዶች ለብስክሌት ተጠቃሚዎች ምቹ የሆነ ጉዞን እና በከፍተኛ ፍጥነት ማሽከርከር እድልን የሚሰጥ ነው፡፡ የአሽከርካሪዎች አውታረመረብ አውታረ መረብለ መኪና አሽከርካሪዎች መዳረሻን የሚሰጥ ሲሆን በአንፃራዊ በአቅራቢያ ላይ ያለን እንቅስቃሴ ግን የሚያመለክት አይደለም፡፡