የግላዊነት ፖሊሲ
ቀን፡- 26/12/2013 ዓ/ም
ይህንን የግላዊነት መግለጫ ያቀረብንበት አላማ የእናንተን የግል መረጃዎች በድህረ ገጾቻችን፣ በሞባይል መተግበሪያዎቻችን፣ በኢሜይል ልውውጦቻችን ወይም በሌሎች በኦንላይን እና በኦፍላይን አውታሮች በምን አይነት መንገድ እንደምንሰበስብ፣ እንደምንጠቀም፣ እንደምናጋራ፣ እንዲሁም በሌላ አግባብ በምን መንገድ እንደምናሳልጥ ለማስገንዘብ ነው፡፡
መረጃዎች በUN Habitat፣ በ Institute for Transportation and Development Policy፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ከተማ ልማት እና ግንባታ ሚኒስቴር አማካኝነት ሊሰበሰቡ ወይም ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፡፡
መረጃው በ UN Habitat ፣ በትራንስፖርትና ልማት ፖሊሲ ኢንስቲትዩት እንዲሁም በኢትዮጵያ ከተማ ልማት እና ግንባታ ሚኒስቴር አማካኝነት ሊሰበሰቡ ወይም ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፡፡
የምንሰበስባቸው መረጃዎች ምንድን ናቸው? | መረጃዎችን በኩኪ አማካኝነት ልንሰበስብ የምንችል ሲሆን እነዚህም የብሮዘርር መረጃዎች፣ መገኛ እንዲሁም የመሳሪያውን አይነት እና የአይፒ አድራሻ ያጠቃልላሉ፡፡ ነገር ግን ድህረ ገጾቻችን የሶስተኛ ወገን መተግበሪያ – ስትሪት ሚክስ የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ አንዳንድ መስተጋብሮችን ከእኛ ሳይቶች ውጪ ሊደረጉ የሚችሉ ሲሆን በእነዚህ ሳይቶች አማካኝነት በሚሰበሰቡ እና ወይም ወደነዚህ ሳይቶች በሚቀርቡት መረጃዎች ላይ ምንም አይነት ቁጥጥር የለንም፡፡ |
የእርስዎን መረጃ በምን አይነት መንገድ እናጋራለን? | የግል መረጃዎች ለሶስተኛ ወገን ቷቋማት አይጋሩም፡፡ ነገር ግን የተተነተኑ የምርመራ ውጤቶች እና መረጃዎች ለአጋር ድርጅቶቻችን እንዲሁም ለሰፊው ታዳሚ ወይም ተጠቃሚዎች ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ ሶስተኛ ወገኖች እራሳቸውን ችለው ነፃ በሆነ ግብይት ምርቶቻቸውን እና አገልግሎቶቻቸውን በቀጥታ ለእርስዎ ተደራሽ ማድረግ እንዲችሉ መረጃዎችን ለሶስተኛ ወገን አንሸጥም ወይም አናጋራም፡፡ |
የእርስዎን መረጃዎች በምን መንገድ እንጠብቃለን እንዲሁም እናከማቻለን? | የእርስዎን የግል መረጃዎች ካልተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎች ለመጠበቅ አላማ ምክንያታዊ የሆኑ የአስተዳደር፣ የቴክኒክ እና አካላዊ የደህንነት እርምጃዎችን እንጠቀማለን፡፡ |
የመረጃ ጥበቃ ድንጋጌዎች | በህግ ሚፈቀደው አግባብ መሰረት የእርስዎን መረጃዎች ከሚነኙበት ሀገር ውጪ ልናጋራ እንችላለን፡፡ በግል ደረጃ ሊለዩ የሚችሉ መረጃዎችን ሊያቀርቡልን የሚፈልጉ ከሆነ እነዚህን መረጃዎች ለአጋሮቻችን እንዲሁም ለድጋፍ ሰጪዎቻችን ወይም ለሌሎች ሶስተኛ ወገኖች ከሀገር ውጪ እንዲሁም በሀገር ውስጥ ልናጋራቸው እንችላለን፡፡ ድህረ ገጾቻችን የሚጎበኙት ከአውሮፓ ሕበረት ግዛት ወይም ከሌላ ክልል ከሆነ እና የመረጃዎች አሰባሰብ እና አጠቃቀምን የሚዳኘው የአካባቢው ህግ ከዩናይትድ ስቴት ህግ የሚለይ ከሆነ እባክዎትን ልብ ይበሉ፡፡ በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ተግባራዊ የማይሆኑ የዳታ ጥበቃ ህጎችን ወደማይጠቀሙ ወደ ሌላ ግዛት እያጋሩ ነው፡፡ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ በአውሮፓ ኮሚሽን አማካኝነት የተረጋገጡ የውል አንቀጾችን የምንጠቀም ሲሆን ይህም የግል መረጃዎች ከአውሮፓ ሕብረት ወደ ዩናይትድ ስቴት እና ወደ ሌሎች ሀገሮች በምናዘዋውርበት ጊዜ ህጋዊ በሆነ አግባብ እንዲዘዋወር ለማስቻል የምንጠቀመው ነው፡፡ ለእነዚህ ስጋቶች (ሪስኮች) እውቅና በመስጠት የግል መረጃዎ በምን አግባብ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይገልጻሉ፡፡ መረጃዎች በኢትዮጵያ፣ በኬኒያ እና በዩናይትድ ስቴትስ ደረጃ ሊሳለጡ ይችላሉ፡፡ |
የእርስዎ መብት | የእርስዎን መረጃ እየተጠቀምን ስለመሆናችን የማወቅ መብት ይኖርዎታል፡፡ በተጨማሪም ያለ ምንም ክፍያ ጥያቄ በማቅረብ መረጃውን ማግኘት፣ ማስተካከል፣ መሰረዝ ይችላሉ እንዲሁም ተግባራዊ በሚሆነው ህግ መሰረት መረጃውን መጠቀም ይችላሉ፡፡ |
ጥያቄዎች | ስለዚህ የግላዊነት መግለጫ ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች ካሉዎት እባክዎን በስልክ ቁጥር 0115-531688 / 0115-154580 / 0115-157952 ያግኙን፡፡ |
ኩኪ (Cookies) እና መሰል ቴክኖሎጂዎች
“ኩኪ” አነስተኛ ይዘት ያለው የጽሁፍ ፋይል ሲሆን በሳይቶች ላይ የተከናወኑ ልምምዶች መረጃን ለመሰብሰብ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በሳይቱ ውስጥ ያሉትን ገጾች በሚጎበኝበት ጊዜ ኩኪ በተጠቃሚው አካል ማሽን ውስጥ በመቀመጥ (ተጠቃሚው ኩኪውን የሚቀበል ከሆነ) ወይም ተጠቃሚው በፊት ሳይቱን ጎብኝቶት ከሆነ መረጃዎችን ያነባል፡፡ ከኩኪዎች የሚሰበሰቡ መረጃዎችን ለማርኬቲንግ እና ሌሎች ለመረጃ አላማ ልንገለገልባቸው እንችላለን፡፡ የተሰበሰቡትን መረጃዎች በአጠቃላይ ለሌሎች ሶስተኛ ወገኖች ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ ብሮዘሮች የሚላኩ “ዱኖት ትራክ” መልዕክቶችን አንቀበልም፡፡ ነገር ግን የሚፈልጉትን የአውታረመረብ ማስታወቂያ networkadvertising.org/choices ላይ መጎብኘት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ኩኪዎችን በሚረከቡበት ጊዜ የሚጠቀሙበት ብሮዘር እንዲያሳውቅዎት ሊያደርጉ ይችላሉ ወይም ብሮዘርዎ ኩኪውን እንዳይቀበል ማድረግ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ይህንን በሚያደርጉበት ጊዜ በሳይቶች ላይ የሚለቀቁ ግላዊ የሆኑ እርስዎን የሚመለከቱ መረጃዎችን ላያገኙ ወይም ላይጠቀሙ ይችላሉ፡፡ የተለያዩ ኩኪዎች የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ሲሆን እነዚህም ከዚህ በታች ተብራርተዋል፡፡
- በጥብቅ አስፈላጊ የሆኑ፡- አንዳንድ ኩኪዎች በሳይቶቻችን ላይ ባሹት መንገድ መጠቀም እንዲችሉ እንዲሁም ሌሎች በሳይቱ ላይ ያሉ ገጽታዎችን ለምሳሌ ጥብቅ የሆኑ የሳይቱ ይዘቶችን መጎብኘት እንዲችሉ የሚያደርጉ መሰረታዊ ኩኪዎች ናቸው፡፡ ያለነዚህ ኩኪዎች በሚጠቀሙት መሳሪያ (ዲቫይዝ) አይነት መሰረት ለእርስዎ ተገቢ የሆነ ይዘትን ማቅረብ አንችልም፡፡
- አሰሳ ና ተግባራዊነት፡- እነዚህ ኩኪዎች ከሳይቱ ጋር በተያያዘ ያከናወኗቸውን ምርጫዎች ለምሳሌ የቋንቋ ምርጫዎን እንዲሁም ፍላጎትዎን እና በልዩ ሁኔታ ለእርስዎ ፍላጎት ምቹ በሆነ መልኩ የተመረጡ ገጽታዎችን ማስታወስ እንድንችል ይረዳል፡፡
- አፈጻጸምና ትንታኔ፡- ሳይቶቻችን ጉግል አናላይቲክስ በመጠቀም ተጠቃሚዎች በምን አይነት መንገድ ሳይቶቻችንን እንደተጠቀሙ ይተነትናሉ፡፡ መሳሪያው እነዚህን ኩኪዎች በመጠቀም ሳይቱን በምን አይነት መንገድ እንደተጠቀሙ መረጃዎችን ይሰበስባል፡፡ (እነዚህም የአይፒ አድራሻዎች፣ የኦፕሬቲንግ ሲስተሞች፣ የብሮዘር አይነቶች፣ ቋንቋዎች እና ያሳለጧቸው ድህረ ገጾችን ይጨምራሉ)፡፡ ከዚህም ሂደት በኋላ እነዚህን መረጃዎች ወደ ጉግል የሚያስተላልፉ ይሆናል፡፡ እነዚህም መረጃዎች ጎብኚዎች በምን አይነት መንገድ ሳይቱን እንደተጠቀሙት ለመገምገም እና ስለ ሳይቱ ክንውኖችን የስታቲክስ ሪፖርቶችን ለማጠናቀር ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ እነዚህም ሪፖርቶች የኦንላይን እንቅስቃሴዎቸን ለመቆጣጠር እና የሳይቱን ትግበራ ለማሻሻል እንጠቀምባቸዋለን፡፡ በተጨማሪም ጉግል የተሟላ የግላዊነት ፖሊሲ እና መመሪያዎችን በተለይ ከጉግል አናላይቲክስ ምርጫ ጋር በተያያዘ ያቀርባል፡፡ እባክዎትን ልብ ይበሉ የጉግል አናላይሲስ ኦፕትአውት ብሮዘር አድ ኦን መረጃዎች ወደ ሳይቱ እንዳይላኩ የማይከለክሉ ናቸው፡፡ ወይም በሌላ አባባል እነዚህ በራሳቸው መረጃዎች ለድህረ ገጽ ትንተና እንዳይውሉ የማይከለክሉ ናቸው፡፡
በተቻለ መጠን ማንኛውም ሶስተኛ ወገን የስታቲክስ ትንተና መረጃዎች እንዳይጠቀሙ ወይም በእኛ ሳይት ላይ የተከናወኑ የጎብኚዎችን ግላዊ መረጃዎችን (እንደ ስም፣ የኢሜይል አድራሻ የቢሊንግ መረጃዎች) ያለፍቃድዎ እንዳይሰበስቡ ለመከልከል ጥረት እናደርጋለን፡፡ ጉግል የእናንተን የግል መረጃ በጉግል አማካኝነት ከተሰበሰቡ ከሌሎች መረጃዎች አይፒ አድራሻ ጋር አያስተሳስርም፡፡ በተጨማሪም እኛም ሆንን ጉግል የእናንተን የአይፒ አድራሻዎች ከኮምፕዩተር ተጠቃሚ ግለሰቦች ማንነት ጋር አናስተሳስርም ወይም ለማስተሳሰር ምንም አይነት ጥረት አናደርግም፡፡ በዚህ ሳይት አማካኝነት የተሰበሰቡ ግላዊ መረጃዎችን ከሌሎች ምንጮች ከተገኙ ግላዊ መረጃዎች ጋር የማናስተሳስር ይሆናል፡፡ በተለይም ተጠቃሚዎች በድህረ ገጻቸው ላይ ቅጽን በሚሞሉበት ጊዜ ግልጽ በሆነ አግባብ መረጃዎቻቸውን ካልሰጡ በስተቀር የሳይቱን ግላዊ መረጃዎች ከሌሎች ምንጮች ጋር የማናስተሳስር ይሆናል፡፡
በተጨማሪም ዌብ ቢከን (በተጨማሪም “ክሊር ጊፍት”፣ “ዌብ ባግስ” ወይም “ፒክስል ታግስ” በመባል ይታወቃሉ) የምንጠቀም ሲሆን እነዚህም ትንንሽ የሆኑ ግራፊክስ ሲሆኑ ልዩ ልዩ መለያዎች ያሏቸው እና ከኩኪ ጋር ተመሳሳይ ተግባርን የሚሰጡ እንዲሁም የሳይቶቹን የተለያዩ ገጾች የጎበኙ ተጠቃሚዎችን ለመቁጠር ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ በተጨማሪም የማስተዋወቂያ ክንውኖች ምን ያህል ውጤታማ መሆናቸውን ለማስላት ወይም ለመገምገም ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ በኤችቲኤምኤል ፎርማት የኢሜይል መልዕከቶች በሚላኩበት ጊዜ ዌብ ቤከኖች ኢሜይሉ መከፈት ያለመከፈቱን እንዲሁም መች እንደተከፈተ ለመልዕክቱ ላኪ የሚያሳውቁ ኩኪዎች ናቸው፡፡ ከኩኪ በተቃራኒ ዌብ ቤከኖች ስውር በሆነ መልኩ ድህረ ገጾች ላይ የሚቀመጡ ሲሆን ኩኪዎች ግን የተጠቃሚዎች የኮምፕዩተር ሀርድ ድራይቭ ላይ የሚከማቹ ይሆናል፡፡
መረጃዎችን ማጋራት እና ይፋ ማድረግ
የተጠቃሚ ማንነትን የማይለዩ መረጃዎች
የተጠቃሚ ማንነትን የማይለዩ መረጃዎችን ከላይ በተጠቀሱት አግባብ ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡ እነዚህን ማንነት የማይለዩ መረጃዎችንም ለሶስተኛ አካላት ልናጋራ እንችላለን፡፡
የልጆች መረጃ አሰባሰብ እና አጠቃቀም
ሳይቶቻችን በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ካሉ ከ13 አመት ወይም ከ16 አመት በቻች ካሉ ልጆች ማንኛውንም የግል መረጃ የማይሰበስቡ ልጆችን ተደራሽ የሚያደርጉ መረጃዎችን የማይጠቀሙ ይሆናል፡፡ እነዚህ መረጃዎች ወደ ሳይቶቻችን መላካቸውን በምንረዳበት ጊዜ የምናጠፋቸው ወይም የምንሰርዛቸው ይሆናል፡፡
ፎረሞች፣ ቻት ሩሞች እና ሌሎች
እባክዎትን ያስታውሱ በማንኛውም ቻትሩም፣ ፎረም፣ ወይም በሌሎች የህዝብ መልዕክት መለጠፊያ መደላድሎች ላይ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚልኳቸው መልዕክቶች ለሌሎች አካላት ይፋ ይሆናሉ፡፡ ሌሎች ሰዎች የእናንተን የኢሜይል አድራሻ እንዳያውቁ የሚፈልጉ ከሆነ ለህዝብ ይፋ በሚያደርጓቸው ማንኛቸውም መልዕክቶች ላይ የኢሜይል አድራሻችሁን ይፋ አያድርጉ፡፡
እባክዎትን በቻትሩም፣ ፎረም እና ፐብሊክ ፖስቲንግ ቦታዎችላይ ይፋ ስለሚያደርጓቸው ማንኛቸውም መረጃዎች በአጽናኦት ልብ ይበሉ፡፡ በተጨማሪም በቻትሩም፣ በፎረም እና በሌሎች የህዝብ መለጠፊያ መደላድሎች ላይ ሌሎች ይፋ ስለሚያደርጓቸው መረጃዎች ኃላፊነትን የማንወስድ ይሆናል፡፡
የሶስተኛ ወገን ድህረገጾች እና የማህበራዊ ሚዲያ አዝራሮች
እነዚህ የግላዊ መረጃዎች ከሳይቶች ላይ ለሚሰበሰቡ መረጃዎች ብቻ ተግባራዊ የሚሆኑ ናቸው፡፡ ሳይቶቹ ወደ ሌሎች ድህረገጾች የሚያገኛኑ ማስፈንጠሪያዎችን የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም በሳይቱ ላይ ሊኖሩ ለሚችሉ ለሌሎች ድህረገጾች ይዘቶች የግላዊነት አተገባበር ኃላፊነትን የማንወስድ ይሆናል፡፡
ከዚህ በታች ያሉትን የማኅበራዊ ሚዲያዎች ፕላግኢን፤ ፌስ ቡክና ቲዊተርን እንጠቀማለን፡፡ ፕላግኢኖቹ በየማኅበራዊ ሚዲያ አውታረ መረቦች ሎጎ አማካኝነት ሊለዩ ይችላሉ፡፡
እነዚህንም ፕላግኢኖች ተግባራዊ የምናደርገው ቱክሊክ በተባለው መንገድ ነው፡፡ ይህም ማለት ሳይቶቻችንን በሚጠቀሙበት ጊዜ ግላዊ መረጃዎች በእነዚህ ማኅበራዊ ሚዲያ ፕላግኢኖች መጀመሪያ ላይ የማይሰበሰቡ ሲሆን ነገር ግን ፕላግኢኖቹ አንድ ጊዜ በሚጫኑበት ጊዜ የግላዊ መረጃዎች የሚዘዋወሩ ይሆናል፡፡ ፕላግኢኖቹን ንቁ በሚያደርጉበት ጊዜ መረጃዎች ወዲያውኑ በፍጥነት ወደ ፕላግኢን ሰጪዎች ይዘዋወሩና የሚከማቹ ይሆናል፡፡ በመሆኑም በአቅራቢዎቹ አማካኝነት በሚሰበሰቡት እና በሚሳለጡት መረጃዎች ላይ ቁጥጥር ማድረግ የማንችል ሲሆን ለተጨማሪ የተሰበሰቡትን መረጃዎች ሙሉ ይዘት፣ ዓላማ እንደዚሁም ለምን ያህል ግዜ እንደሚቆዩ ግንዛቤው የለንም፡፡
በፕላግኢን አቅራቢዎች አማካኝነት የሚሰበሰቡና የሚሳለጡ መረጃዎች ዓላማና ስፋት በፕላግኢን አቅራቢዎች የግላዊነት ፖሊሲ ላይ ተቀምጧል፡፡ በእነዚህም ፖሊሲዎች ላይ የእናንተን መብት እና የግላዊነት መረጃ ጥበቃ መጫወትን ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡
ፌስቡክ ኢንኮርፖርሽን፣ 1601 ዊሎው ጎዳና፣ ሜንሎው ፓርክ፣ ካሊፎርኒያ 94304፣ ዩኤስኤ፡ https://www.facebook.com/privacy/explanation.
ቲዊተር ኢንኮርፖሬሽን፣ 1355 ማርኮት ጎዳና፣ ሱቲ 900፣ ሳንፍራንሲስኮ፣ ካሊፎርኒያ 94103፣ ዩኤስኤ፡ https://twitter.com/privacy .
ተጠቃሚዎች ስትሪትሚክስ ድህረገፆችን በሚጠቀሙበት ጊዜ ይህም በተመሳሳይ መልኩ ተፈፃሚ ይደረጋል፡፡ እነዚህንም ድህረገፆች በመጠቀም የጎዳናዎች ክሮስሴክሽኖችን መረጃ የምንሰበስብ ይሆናል፡፡
የእርስዎ የግል መብቶች
የእርስዎን መረጃዎች ቅጂ ለመጠየቅ፣ ለማረም፣ ለመሰረዝ ወይም አጠቃቀሙን ለመወሰን ወይም እነዚህ መረጃዎች ወደ ሌሎች ተቋማት እንዲዘዋወሩ ጥያቄ የማቅረብ መብት ይኖራችኋል፡፡ በተጨማሪም አንድ አንድ ክንውኖች ላይ ጥያቄ የማቅረብ መብት ይኖርዎታል፡፡ እነዚህንም ክንውኖች እንዳይፈፀሙ ለመከልከል የእናንተን ፈቃድ የምንጠይቅ ይሆናል፡፡ እነዚህ መብቶች በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ የተወሰኑ ሲሆን ለምሳሌ የእናንተን መረጃዎች በመጠቀም በሕግ የሚፈለጉ መረጃዎችን ለማሳለጥ ዓላማ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፡፡ ይህ በሚፈጠርበት ጊዜ ምንም እንኳን እናንተ ፈቃዳችሁን ባትሰጡም መረጃችሁን አሳልፈን መስጠታችንን የምንቀጥል ወይም የምናቆይ ይሆናል፡፡
ከእናንተ መረጃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ያላችሁን ጥያቄዎች በሙሉ መመለስ የቻልን እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ የእናንተን መረጃ ከምናሳልጥበት መንገድ ጋር በተያያዘ ማንኛውም አይነት ስጋት ቢኖርዎ እባክዎትን ያግኙን፡፡
ጥያቄዎ ያልተፈታ እንደሆነ ለመረጃ ጥበቃ ባለስልጣን ቅሬታዎን የማቅረብ መብት ይኖርዎታል፡፡
ምደባ
የእኛ ንብረቶች ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ለሌላ ወገን ወይም አካል በሚዘዋወሩበት ጊዜ ወይም ከሌሎች ተቋማት ጋር በሚዋሀዱበት ጊዜ ከእርስዎ ግላዊ መረጃዎች ወይም ግላዊ ባልሆኑ መረጃዎች ጋር በተያያዘ የማጋራት ፍላጎትዎን የሚያሳውቁን ይሆናል፡፡
የዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ለውጥ
ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህንን የግላዊነት ፖሊሲ የመለወጥ ሙሉ መብት አለን፡፡ ይህንን በምናደርግበት ጊዜ ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ሳይት ላይ የተሰበሰቡ መረጃዎችን በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ የመጀመሪያ ክፍል ላይ ማስቀመጥ የምንችል ይሆናል፡፡ ከዚህ ፖሊሲ ጋር በተያያዘ የማንኛውም የመሣሪያ ለውጥ በምናደርግበት ጊዜ በአካውንታችሁ ላይ በሰጣችሁን የመጀመሪያ የኢሜይል አድራሻ አማካኝነት የምናሳውቃችሁ ይሆናል፡፡ ወይም በሳይቱ ዋነኛ ክፍል ላይ የምናስቀምጥ ይሆናል፡፡
ጥበቃና መረጃዎችን የማቆየት አሠራር
በኢንተርኔት ላይ የሚዘዋወሩ የመረጃ ስርጭቶች 100% ዋስትና ሊሰጣቸው አይችልም፡፡ በተለይ ወደ እኛ ስለሚልኳቸው ማንኛውም መረጃዎች ጥበቃ ዋስትና የማንሰጥ ሲሆን እርስዎምም ማንኛውንም መረጃ ወደ እኛ በምታዘዋውሩበት ጊዜ በራሳችሁ ስጋት (ሪስክ) አማካኝነት መሆኑ እውቅና መስጠት ይኖርባችኋል፡፡
የመረጃ ዝውውርን ካከናወኑ በኋላ ከሲስተማችን ጋር በተያያዘ የጥንቃቄ እና ጥበቃ ሂደቶችን ለማድረግ የተቻለንን ምክንያታዊ ጥረቶች የምናደርግ ይሆናል፡፡ የእናንተን መረጃዎች ካልተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎች ለመጠበቅ ወይም ለሌላ አካላት ይፋ እንዳይሆኑ ለመከላከል ፋይርዎልን የምንጠቀም ይሆናል፡፡ ነገር ግን እባክዎ ልብ ይበሉ ይህ ማለት በፋይርዎል አማካኝነት ወይም በሌሎች የጥበቃ ሶፍትዌሮች አማካኝነት የሚጠበቁ መረጃዎች ለሌሎች ይፋ አይደረጉም ወይም አይለወጡም ወይም እነዚህ ሶፍትዌሮች መሰበር አይችሉም ማለት አይደለም፡፡
የእኛ የጥበቃ ሲስተሞች መጣሳቸውን በምንረዳበት ጊዜ ተገቢውን የሆነ እርምጃ መውሰድ እንዲችሉ በኤሌክትሮኒክ አማካኝነት እርስዎን ለማሳወቅ ጥረት የምናደርግ ይሆናል፡፡ ሳይቶችን በመጠቀም ወይም ግላዊ መረጃዎችን በማቅረብ በኤሌክትሮኒክ አውታሮች ከጥበቃ፣ ከግላዊነት እንዲሁም ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከእናንተ ጋር የመረጃ ልውውጦችን እንድናደርግ የምትስማሙ ይሆናል፡፡ የጥበቃ ሶፍትዌሮች በሚጣሱበት ወይም በሚሰበሩበት ጊዜ የዚህን ማሳሰቢያ በሳይቶቻችን ላይ የምንለጥፍ ይሆናል፡፡ በተጨማሪ የዚህን መረጃ በሰጣችሁን የኢሜይል አድራሻ አማካኝነት የምናሳውቃችሁ ይሆናል፡፡ በሚኖሩበት ቦታ ሁኔታ የጥበቃ ሶፍትዌሮች ጥሰትን በጽሑፍ ማሳሰቢያ አማካኝነት መልዕክት መቀበል የሚችሉ ይሆናል፡፡
በዚህ የግላዊነት መመሪያ ውስጥ የተቀመጡትን ዓላማዎች ለመፈጸም የእርስዎን PII አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ እናቆየዋለን። ሕጎች የተወሰኑ መረጃዎችን ለተወሰኑ ጊዜያት እንድንይዝ ሊጠይቁን ይችላሉ።
ዳኝነት እና የደረጃ ትግበራ
ከዚህ ሳይት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ወይም ከጥሰት፣ ከተፈፃሚነት፣ ከአፈታት ወይም ከግላዊ ፖሊሲዎች ሕጋዊነት ወይም ከዚህ ይዘት ጋር ተያያዥነት ካላቸው ጉዳዮች ጋር በተያያዝ ማንኛውም ልዩነት፣ ጥያቄ፣ እርምጃ ወይም ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ ሁለቱ ወገኖች ግጭቶቻቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት በቅን ልቦና በመጀመሪያ ደረጃ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ከአንደኛው ወገን ለሌላኛው ወገን የጽሑፍ ማሳሰቢያን በመስጠት እና ስለ ግጭቱ ሃተታ በመግለጽ ሌላኛው ወገን በ30 ቀናት ውስጥ ግጭቱ ስለሚፈታበት አግባብ ውሳኔን እንዲያስተላልፍ ምላሹን በመጠየቅ የሚከናወን ነው፡፡ ማሳሰቢያዎች መላክ የሚኖርባቸው በግንኙነት አድራሻዎቻችን መረጃ አማካኝነት መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህም መረጃዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊሻሻሉ ይችላሉ፡፡
እነዚህ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ማንኛውም ሕጋዊ እርምጃዎች ወይም የክስ ሂደቶች ከመወሰዳቸው በፊት ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባቸው የመጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ ናቸው፡፡
ማንኛውም ግጭት ከላይ በተገለፀው አግባብ መፈታት የሚችል ከሆነ ብቸኛ ዳኝነት የሚሰጠው ተቀባይነት በሚኖራቸው ገላጋይ ዳኞች እና በየግል ደረጃ በሚወሰኑ ዳኞች ውሳኔ አማካኝነት ነው፡፡ በየግል ደረጃ የሚወሰኑ ገላጋይ ዳኞች ማለት እርስዎ በግልዎ ደረጃ ለሚጠይቁት ጥያቄ ዳኝነት ማስተላለፍን የማይችሉ መሆንዎን የሚገልጽ እና በማንኛውም ሂደት ውስጥ በማንኛውም አቅም ተወክለው መቅረብ የማይችሉ መሆንዎን የሚያመለክት ነው፡፡ በዳኝነት ጊዜ በፍርድ ቤት ደረጃ የሚኖርዎት ሌሎች መብቶች ማለትም ይግባኞችን የማቅረብ መብትን ጨምሮ እንዲወሰኑ የሚደረግ ይሆናል፡፡