ደንብና ሁኔታዎች
የተቀናጀ የኢትዮጵያ ጎዳና ዲዛይን ቱል በከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አማካኝነት ከUN Habitat፣፣ UNRSF (ዩኤንአርኤስኤፍ) እንዲሁም ከITDP (አይቲዲፒ) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን በኢትዮጵያ ያሉ ባለሙያዎችና ተጠቃሚዎች የተቀናጀ የኢትዮጵያ ዲዛይን መመሪያን መሰረት በማድረግ የጎዳና ክፍሎች ዲዛይን ለመስራትና በምስል ለማየት እንዲያስችላቸው የተዘጋጀ ነው።
ቱሎቹ ተጠቃሚዎች ዲዛይኖቻቸውን መመልከት ከሚችሉባቸው እንዲሁም በሚፈቀደው መመሪያ መሠረት በሚፈለገው ዝርዝር መሠረት እንዲያስተካክሉ ማድረግ ከሚችሉባቸው ከስትሪት ሚክስ ጋር ትስስር ያላቸው ናቸው፡፡ በዚህ ሳይት አማካኝነት የሚቀርቡ የክሮስሴክሽን ቴምፕሌት ወይም ዲዛይኖች በማንኛውም መንገድ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ማረጋገጫ ወይም ፈቃድን በማንኛውም መንገድ የማይሰጥ ወይም የማያረጋግጥ ነው፡፡ የዲዛይን ትግበራዎች ተግባራዊ በሚሆን ድንጋጌዎች ወይም በማረጋገጫ ሂደቶች አካሄድ መሠረት ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሊላኩ ይገባል፡፡
ቱሎቹ ከዲዛይኑ ትክክለኛነት ጋር በተያያዘ በተለይም ተግባራዊ ከተደረጉ ሕጎች መጣጣም ጋር በተያያዘ ማንኛውንም ማረጋገጫ የማያቀርብ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የቱሉ ተጠቃሚዎች አስፈላጊ የሆኑ ድንጋጌዎችን በሙሉ እንዲያነቡ እና ሕጎቹን መከተላቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
እነዚህ ቱሎች ጥራታቸውን ለማሻሻል አላማ እና በባለድርሻ አካላት ምክረ ሃሳብ መሠረት ከሌሎች ማንዋሎች ለውጥ ጋር ለማዘመን ዓላማ ሊለወጡ፣ ሊሻሻሉ ወይም ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ቱሎቹ ማንኛውንም አይነት ማሳሰቢያ ለተጠቃሚዎች መስጠት ሳያስፈልግ ሊሰረዙ ወይም ሊሻሩ ይችላሉ፡፡