የተሟላ የአውታረ መረብ መዋቀር
የተሟሉ ጎዳናዎች እና አውታረ መረቦች ከትራፊክ አደጋዎች ነፃ እና ለሰዎች እንቅስቃሴ ምቹ የሆኑ መረማመጃ ክፍሎችን እንዲሁም ዝቅተኛ የሆነ የግሪንሃውስ ጋዞች ልቅትን የመፍጠር አቅም አላቸው፡፡ በተጨማሪም የጎዳና አውታረ መረቦች ለረጃጅም ጉዞዎች ከፍተኛ ጥራት ላለው የሕዝብ ትራንስፖርት እና በዝግተኛ ፍጥነት ለሚንቀሳቀሱ የሞተር እንቅስቃሴዎች የሚያመቻቹ መሆን አለባቸው፡፡
ይህ ክፍል እንዴት ለእግረኞች፣ ለብስክሌተኞች እንዲሁም ለሕዝብ ትራንስፖርቶች ቅድሚያ የሚሰጡ አውታረ መረቦች የሚሰሩበትን ሂደቶችን የሚያስቃኝ ነው፡፡ የሞተር ተሽከርካሪዎች በዚህ ውስጥ የሚካተቱ ቢሆንም በከፊል ደረጃ ብቻተቀባይነት የሚኖራቸው ይሆናል፡፡
የሞዳል ቅደም ተከተል
የከተማዎች ውስጥ የሕዝብ የጎዳና ቦታዎች ዲዛይን እና አጠቃቀምን በተመለከተ የሚሰጡ ውሳኔዎች ለእግረኞች መረማመጃ ቦታ፣ ለሳይክል አሽከርካሪዎች እንዲሁም ለሕዝብ ትራንስፖርት ፍላጎቶች ቅደም ተከተል በመከተል ውሳኔ ሊሰጡ ይገባል፡፡
ውጤታማ ለሆነ እንቅስቃሴ ዘለቄታዊ መፍትሄ ለማግኘት ከፍተኛ ጥራት ላላቸው የሕዝብ ትራንስፖርት እና ለኤንኤንቲ መገልገያዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከፍታቸው ከፍተኛ በሆነ አውራ ጎዳናዎች ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች የመንገድ መዘጋጋትን በጊዜያዊነት ሊቀንስ ይችላል፡፡ ነገር ግን ዘለቄታዊ መፍትሄ የሚሆነው ለሰፊው ትራንስፖርት ማለትም እንደ ቢአርቲ ላሉት በቂ የሆነ ቦታ በመመደብ እንዲሁም ለእግረኞች እና ለብስክሌት ፋሲሊቲዎች ምቹ እና በቂ ስፍራ በመስጠት ነው፡፡
የሕዝብ ትራንስፖርት
የተሟላ አውታረ መረብ መነሻ ነጥብ የሚሆነው የሕዝብ ትራንስፖርት ነው፡፡ የሕዝብ ትራንስፖርት በከተማ አካባቢዎች ብዛት ያላቸውን ሰዎች በተቀላጠፈ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማዘዋወር ይረዳሉ፡፡ በተገቢው መንገድ የተሳሰረ የጎዳና አውታረ መረብ የሕዝብ ትራንስፖርቶች ለሁሉም የከተማ ነዋሪዎች እርቀት ምቹ በሆነ መልኩ የሚያሰሩ ናቸው፡፡ የጎዳናዎች አውታረ መረብ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች በቀጥታ መስመር እንዲሁም ዝቅተኛ በሆነ ጉዞ አገልግሎትን መስጠት እንዲችሉ ያስችላሉ፡፡ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያላቸው ኮሪደሮች ባስራፒድ ትራንዚት (ቢአርቲ) ራይት ኦፍ ዌይ አገልግሎትን የሚሰጡ የባሶች መተላለፊያ የሚፈቅዱ ናቸው፡፡ መደበኛ የባስ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ኮሪደሮች የጎዳናዎች ዲዛይን በምልክቶች ወይም ደህንነቱ በተጠበቀ የእግረኞች ማቋረጫ መንገድ አማካኝነት ለህዝብ ትራንስፖርቶች ምቹ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ የህዝብ ትራንስፖርቶች መስመር እና ማቆሚያዎች ሚዛናዊ በሆነ ፍጥነት ተግባራዊ ሊደረጉ ይገባል (ለምሳሌ የቢአርቲ ባስ)፡፡
የእግር መንገድ
የእግር መንገድ በኢትዮጵያ ከተሞች ላይ በስፋት የሚስተዋሉ እና የሕዝብ ትራንስፖርት ጉዞዎችም በእግር ጉዞ ጀምረው በእግር ጉዞ የሚጠናቀቁ ናቸው፡፡ ጤነኛ የሆነ እና ከአየር ብክለት የፀዳ እንቅስቃሴ እንዲሁም የመዝናኛ ልምዶች እና የእግረኛ መንገዶች ለከተማ ህይወት ቁልፍ ሚና ያላቸው ናቸው፡፡ የእግረኞች አውታረ መረቦች ከተሽከርካሪዎች ትራፊክ ነፃ በሆነ ወይም በተጠበቀ መልኩ ለሁሉም መዳረሻ ስፍራዎች ግንኙነት ያላቸው እና የተሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ከዚህ በታች ያሉት ምስሎች ትራንዚትን መሠረት ያደረጉ ዲስትሪክቶችን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ በስተግራ በኩል ያለው የቢአርቲ ሥርዓት ሲሆን ከአርቴሪያል የጎዳና አውታረ መረብ ጋር ተያያዥነት ያለው ነው፡፡ በስተቀኝ በኩል ያለው የባቡር መንገድን መሠረት ያደረገ ሥርዓትን የሚከተል ሲሆን የጎዳናዎች ትስስርን የማይፈቅድ ነው፡፡ ሁለቱም የጎዳናዎች አውታረ መረብ ያላቸው እና ወደተለያዩ የትራንዚት ክፍሎች የሚያገናኙ ናቸው፡፡ ሁለቱም ዲያግራሞች የ5 ደቂቃ (የ400 ሜትር) የእግረኛ ራዲየሶችን የሚጠቀሙ ናቸው፡፡
ብስክሌት መንዳት
አረንጓዴያማ መንገዶች፣ መተላለፊያ መንገዶች እንዲሁም ሌሎች ሞተርን የማይፈቅዱ የትራንስፖርት ፋሲሊቲዎች የተሟላ አውታረ መረብን በመስጠት ረገድ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ናቸው፡፡ ብስክሌቶች በዝቅተኛ ወጪ ከአየር ብክለት የፀዳ እንቅስቃሴ እንዲኖር የሚያደርጉ ናቸው፡፡ የብስክሌት እንቅስቃሴ በሁሉም እድሜ ክልል ላሉ ሰዎች ምቹ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እንዲከናወን ከተማዎች የተሟላ የብስክሌት መጓጓዣ መፍቀድ እና ሁሉም መዳረሻ ስፍራዎች ለዚህ መንገድን ማበጀት ይኖርባቸዋል፡፡ የብስክሌት አውታረ መረቦች በርካታ የፋሲሊቲ አይነቶችን ሊይዙ የሚችሉ ሲሆን ዝቅተኛ ፍጥነት ያላቸው የውስጥ ለውስጥ ጎዳናዎች፣ የአውራ ጎዳናዎች ፣ የተለየ የብስክሌት ማሽከርከሪያ ቦታዎች እንዲሁም በፓርኮች እና አረንጓዴያማ ስፍራዎች ውስጥ የተበጁ የብስክሌት ማሽከርከሪያ መንገዶችን ሊይዙ ይችላሉ፡፡ የብስክሌት አውታረ መረቦች ከሕዝብ ትራንስፖርት ሥርዓት እንዲሁም ለእግረኞች ቅድሚያ ከሚሰጥባቸው ቦታዎች ጋር ሊተሳሰሩ ይገባል፡፡ እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ የብስክሌት ማቆሚያ ቦታዎች በሁሉም መዳረሻ ስፍራዎች ላይ ሊኖሩ ይገባል፡፡
ከዚህ በታች ያሉት አረንጓዴያማ እና የብስክሌት ማሽከርከሪያ ጎዳናዎች ያሏቸው የተሟሉ አውታረ መረቦች ናቸው፡፡ በስተግራ በኩል ያለው ምስል የብስክሌት ፋሲሊቲዎች በምን አይነት መንገድ ትይዩ መስመሮች (ግሪድ) መሆን መቻል አለመቻላቸውን የሚያመለክት ነው፡፡ በመንገዶች ኮሪደሮች ዙሪያ ካሉት በተቃራኒ የብስክሌት አውታረ መረቦች የባህር ወይም የባቡር መስመሮችን ተከትለው የተገነቡ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በስተቀኝ በኩል ያለው አረንጓዴያማ መንገድ በቢአርቲ የትራንዚት ትይዩ መስመር መሠረት የተዘረጋ ነው፡፡
የግል ተሽከርካሪዎች
የተሟሉ አውታረ መረቦች ወይም መንገዶች የሞተር ተሽከርካሪዎችን የሚፈቅዱ እና ይህንን በደጋፊንት ሚና የሚያሳልጡ ናቸው፡፡ እነዚህ በመጀመሪያ ደረጃ ለአገልግሎት እና ለስርጭት ዓላማ ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡ ልዩ ልዩ መለኪያዎች ማለትም የመንገድ ላይ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ሰዓት የዝግጊት ቁጥጥሮች እንዲሁም አጠቃላይ የግል ተሽከርካሪ ሞተሮች ቁጥጥር ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህም በአጠቃላይ በግል ተሽከርካሪ ሞተሮች የተደረጉ የኪሎ ሜትር ጉዞዎችን መለካት እና የግል ተሽከርካሪ ሞተሮችን ተጠቃሚነት ወደ 20% ወይም ከዚያ በታች እንዲሆን ማገድ ይኖርባቸዋል፡፡
የሞተረኞች አውታረ መረብ ለከተማ አካባቢዎች አገልግሎትን መስጠት የሚኖርባቸው ሲሆን እነዚህም ለእግረኞች ለብስክሌተኞች እና ለሕዝብ ትራንስፖርቶች ደህንነት እና አጠቃቀም ምቹ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይገባል፡፡ ውጤታማ በሆነ መንገድ የተሳሰረ እና የተደራጀ የሞተር ተሽከርካሪ አውታረ መረቦች የዝግጊት ማነቆዎችን ሊቀንሱ ይችላሉ፡፡ የሁሉንም ተጠቃሚዎች ደህንነት ለማረጋገጥ የሞተር ተሽከርካሪዎች ፍጥነት በትራፊክ መቆጣጠሪያዎች፣ ተገቢ በሆኑ በጎዳናዎች ስፔሲንጎች፣ ደኅንነቱ በተጠበቀ በኢንተርሴክሽን ዲዛይኖች እንዲሁም በአውቶማቲክ ኢንፎርስመንት አማካኝነት ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል፡፡
የተሳሰረ የእግረኛ አውታረ መረብ እና አጫጭር ርዝመት ያለው የጎዳና መንገድ ለውስጥ ለውስጥ መንገዶች አጫጭር እና ከሌሎች ዋና መንገዶች ጋር የሚያገናኙ ቀጥተኛ መንገዶች ያሏቸው ናቸው፡፡ ከላይ በታየው ምሥል ላይ እንደተገለፀው በእነዚህ አካባቢዎች ላይ በእግር መንቀሳቀስ ወይም በብስክሌት መጓጓዝ የተሻለ ነው፡፡ የእነዚህ አካባቢዎች ማዕከላዊ ስፍራዎች አረንጓዴያማ እና ለእግር ጉዞ፣ ለብስክሌተኞች እንዲሁም ለህዝብ ትራንስፖርቶች ምቹ ናቸው፡፡ ጥራቱ በተጠበቀ መልኩ የተከፋፈለ የመንገድ አውታረ መረብ በርካታ መስመሮችን የያዘ እና ወደተለያዩ መዳረሻዎች የሚያደርስ መንገድ ያለው ሲሆን በተጨማሪም በእግር ወይም በብስክሌት ጉዞዎችን ለማድረግ ምቹ ያደርገዋል፡፡ ትልልቅ ህንፃዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች አፍርሶ የመገንባት ሂደት ረጃጅም ህንፃዎችን በመከፋፈል የእግረኞችን መንገድ ትስስር ለማሳለጥ እድልን ይሰጣል፡፡
ኮምፖዚት አውታረ መረብ
በርካታ ክፍሎች ወይም ኮምፖነንቶች በሚኖሩበት ጊዜ ከዚህ በታች ባለው ምሥል በተገለፀው መልኩ ኮምፖዚት አውታረ መረብ ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ጊዜ የመነሻ ነጥብ የሚሆነው የህዝብ ትራንስፖርቶች ቦታ ሲሆን የቢአርቲ ስርዓት (ቀይ) አውታርን መሠረት ያደረገ የመተላለፊያ ዲስትሪክት ወደየጣቢያው የሚያደርሱ የ5 ደቂቃ የነዋሪዎች የመጓዣ መንገዶችን በዋነኝነት የያዙ ናቸው፡፡ ከጣቢያዎቹ በመነሳት ዋነኛ የእግረኞች መንገድ (ቢጫ)፡- ወደ ጣቢያው ለሚሄዱ ሰዎች የተዘጋጁ ቦታዎች ያላቸው እና የእነዚህ አካባቢዎች ምልክትም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የእግረኞች መውጫ መንገድ ከእነዚህ የእግር መንገዶች ጋር የተሳሰሩ እና ለሁሉም ብሎኮች እንዲሁም በአካባቢው ላሉ ዲስትሪክቶች የመገናኛ እድሎችን የሚፈጥሩ ናቸው፡፡ አረንጓዴያማ መተላለፊያዎች (ቢጫ-አረንጓዴ) በአካባቢዎቹ ውስጥ የሚገነቡ እና በተለይም ውሃ በሚኖርባቸው ስፍራዎች የሚዘወተሩ ናቸው፡፡ የብስክሌት መንገዶች (አረንጓዴ) ለብስክሌተኞች በከፍተኛ ፍጥነት መንቀሳቀስ እንዲችሉ እና ምቹ መጓጓዣ የሚፈጥር ነው፡፡
የብስክሌት ማሽከርከሪያ አውታሮች ከቢአርቲ ጣቢያዎች ጋር የተሳሰሩ ይሆናሉ፡፡ የአሽከርካሪዎች አውታረ መረብ ከቦታዎቹ ጋር የተሳሰሩ ቢሆንም የእርስ በእርስ የማይጋጩ እና በማይሳረሱ መልኩ የተገነቡ ይሆናሉ፡፡ ለሁሉም ብሎኮች ወይም ህንፃዎች የመግቢያ መንገዶች የሚገነቡ ሲሆን አሽከርካሪዎች በዙሪያዎቻቸው በሚኖሩ መንገዶች የሚሳለጥ ይሆናል፡፡ የሞተር ተሽከርካሪዎች በውስጥ ለውስጥ መንገዶች እንዲጓዙ የሚፈቀድ ቢሆንም እንደአማራጭነት የሚያዙም ይሆናል፡፡
የጎዳናዎች ደረጃ
የጎዳናዎች ደረጃ አሰጣጥ በማኅበራዊ-ምጣኔ ሃብታዊ ባህርያት፣ በግምታዊ ተጠቃሚዎች ቁጥር እንዲሁም በነባራዊ እና በታሰበው የመሬት አጠቃቀም፣ የመሬት አቀማመጥ እና የጎዳናው ቦታ ላይ በመመስረት በከተማ እቅድ ደረጃ ሥር የሚመደብ ይሆናል፡፡
ብሔራዊ የጎዳናዎች የክፍፍል ሥርዓት ለፈንድ፣ ለሪፖርት እና ለቢሮ ጥቅሞች ሊውል ይችላል፡፡ ምንም እንኳን የከተማዎች ጎዳናዎች በርካታ የትራንስፖርት አውታሮችን የሚፈቅዱ ቢሆንም የአንድ አገልግሎት ጥቅም የመንገዶችን ሕጋዊ ደረጃ አሰጣጥ ሊነካ አይገባም፡፡ ለምሳሌ የቢአርቲ ሥርዓት የሆነው መንገድ ለአርቴሪያል ለሕዝብ ትራንስፖርት ሊሆን ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አርቴሪያል የሆነው ሥርዓት የብስክሌት መጓጓዣዎች መንገድ ካሉት ለብስክሌተኞች በአርቴሪያልነት የሚለይ ይሆናል፡፡ ከዚህ በታች ያሉት የጎዳናዎች አመዳደቦች በዚህ ማንዋል ውስጥ ተካተው ተገልፀዋል፡፡ የየአይነቶቹ ሚና ከዚህ በታች ባለው መልኩ ተገልጿል፡፡
ዋና ጎዳና
ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የባሶች ራፒድ ትራንዚት (ቢአርቲ) ወይም ለባሶች የተለየ መስመርን፣ የሳይክሎች እራሱን የቻለ የተለየ መስመርን እና ከፍተኛ ጥራት ያለው የእግረኞችን ቦታ የያዘ ሰፊ ኮሪደር ነው፡፡
ሰብሳቢ ጎዳና
የትራፊክ እንቅስቃሴዎች በአነስተኛ መልኩ በሚኖሩባቸው ቦታዎች ለብስክሌተኞች እንዲሁም ለእግረኞች የተለየ መንገድ ያለው አማራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት መንገድ ነው፡፡
የአውታረ መረብ ዴንሲቲ
የመንገድ አውታረ መረብ የመንገድ ስፋት የሚፈልግ ሲሆን በእነዚህ አካባቢ የሚኖሩት ብሎኮች የእግር መንገድን ከማሳለጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና ያላቸው ናቸው፡፡ ዋና የማሽከርከሪያ መንገዶች (ለምሳሌ አርተሪያልስ) ሲስተሙ እስካልተጨናነቀ ድረስ በብዛት መኖር ይኖርባቸዋል፡፡ የሕዝብ የትራንስፖርት መስመሮች እና ማቆሚያዎች ሚዛናቸውን በጠበቁ የፍጥነት ወሰኖች መስመሮች ላይ (ለምሳሌ ለቢአርቲ ባሶች) እንዲሁም ለመግቢያ መንገዶች (ለማቆሚያና ለባስ ጣቢያዎች) በሚመች መልኩ በቂ ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
የመንገድ ወይም የመገልገያ ዓይነት | ምደባ | ክፍተት (ሜ) |
የሕዝብ ማመላለሻ | ኤክስፕረስ ማቆሚያ/ጣቢያ መደበኛ ማቆሚያ/ጣቢያ | 600-800 |
ሞተር አልባ ትራንስፖርት | የብስክሌት መንገድ | 150-200 |
ጎዳና (ተሽከርካሪ) | ዋና አርቴሪያል ጎዳና | 1,000-1,500 250-500 |
የመንገድ እና የመሬት አጠቃቀም
መንገዶች የመሬት አጠቃቀም የሚወስኑ እና የከተማ ማዕከሎችን መዋቅር የሚወስኑ ናቸው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የተለያዩ የመሬት አጠቃቀሞች የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ፍላጎትን ይፈጥራሉ፡፡ በመሆኑም መንገዶች፣ የመሬት አጠቃቀም እና ትራንስፖርት የተሳሰሩ ነገሮች ናቸው፡፡ የነዚህም ግንኙነት የከተሞች ባህሪ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው፡፡
ትራንዚት ኦሬንትድ ዲቨሎፕመንት (ቲኦዲ) በተሳሰረ የመሬት አጠቃቀም (ነዋሪዎች፣ እንቅስቃሴዎች እና ክፍት ቦታዎች) መርሆች መሠረት ከተሞችን እና መንደሮችን ከሕዝብ ትራንስፖርት ከእግር መጓጓዣ መንገድ እና ከብስክሌት ማሽከርከሪያ ፋሲሊቲዎች ረገድ የምናቅድበት መንገድ ነው፡፡ ይህም ስኬታማ መሆን የሚችለው የከተሞችን ጥግጊት (ዴንሲቲ)፣ ግንኙነት እንዲሁም ከ5-10 ደቂቃ የሚፈጁ የእግር ርቀት ፈጣን የትራንዚት ጣቢያዎች በማዋቀር እንዲሁም ጥራቱን የጠበቀ የከተማ ቦታ አጠቃቀም ተግባራዊ በማድረግ እንዲሁም ስብጥር የሆነ የመሬት አጠቃቀምን ለሁሉም ተደራሽ በማድረግ የሚመጣ ነው፡፡
ታሪካዊ ጎዳናዎች
በተቻለ መጠን የመንገዶችን ስፋት፣ ይዘት እና ቅርጽ ከአሁን በፊት በነበሩበት መንገድ እንዲጠበቁ የሚደረግበት እና በፊት በተሰራበት መሣሪያዎች እና ቴክኒኮች የሚጠገኑ እና የሚሻሻሉ ናቸው፡፡ ተግባራዊ መሆን በሚችሉባቸው በርካታ ጊዜያት ታሪካዊ መንገዶች የእግር መንገድ እንዲሆኑ ይመከራል፡፡ በታሪካዊ መንገዶች ላይ የሚከናወኑት ተግባራት እንደ ዳንስ ዘፈን እና የተለያዩ ትዕይንቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም የከተሞች ታሪካዊ ማዕከላት ለተለያዩ ክስተቶች እን ፌስቲቫሎች ጊዜያዊ ወይም ቋሚ ቦታን ለእይታ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡